በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ የተለያዩ ጨረታዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የዱቄት ፋብሪካ ሙሉ ሰርቢስ ማድረግ ይፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ለአራተኛ ጊዜ የወጣ የG+5 ህንጻ የሚያአስፈልጉ እቃዎች ሎት 1 የመጋረጃና ቁሳቁስ ከእነ እጁ ሎት 2 የሳውንድ ሲስተም እስከመገጣጠሙ እንዲሁም ሎት 3 ላይት ቦክስ /ዲጅታል ታፔላ/ እስከመገጣጠሙ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፍ የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ ያላቸዉ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- የጨረታው ዋጋ ብር 200,000 /ከሁለት መቶ ሸህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማስያዝ እና የሚሞሉት ዋጋ የቫት የግብይት ከሆነ ከነቫቱ መሆን አለበት፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትን የምታሟሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከዩኒየኑ ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ሂሳብ ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጄው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ለዱቄት ፋብሪካ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ወጥቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን 11፡30 ድረስ መግዛት የሚችሉ ሲሆን በሚቀጥለው ቀን በ11ኛው ቀን 4፡30 የሚከፈት ይሆናል፡፡ ለአራተኛ ጊዜ የወጣ ለG+5 ህንፃ ለተከታታይ 7 ቀናት ወጥቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 7ኛው ቀን 11:30 ድረስ መግዛት ይችላሉ፤ በ8ኛው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
- የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ሥምና የክብ ማህተሙ ሥም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እንዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ሥም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጐልም፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ (ሲፒኦ) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፤ ይህንን ካላደረገ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ብር ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለዱቄት ፋብሪካ ሰርቢስ ማድረጊያ ቦታ ዳሞት ዩኒየን 03 ቀበሌ ከሚገኘው ዱቄት ፋብሪካ ውሰጥ ይሆናል፡፡
- በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
- የማስረከቢያ ቦታ ዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ ቡሬ 03 ቀበሌ ከሚገኘው ዋና ቢሮ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40 /10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡
የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተ