የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት እየተሰጠ ነው

0
21

በአማራ ክልል 3ኛው ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት እየተሰጠ ነው፤ ክትባቱ ከመስከረም 30 ቀን እስከ ጥቅምት 03 ቀን 2018 ዓ.ም ነው የተሰጠው፡፡

በአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከል እና መቆጣጠር ባለሙያ ቢኒያም ከበደ የፖሊዮ በሽታ (የልጅነት ልምሻ) በቫይረስ የሚመጣ ዘላቂ ጉዳትን የሚያስከትል በሽታ መሆኑን አስንዝበዋል፤ ይሁን እንጂ በቀላ መከላል እና መቆጣጠር እንደሚቻልም ነው ያስገነዘቡት፡፡

ክትባት ደግሞ ዋናው መከላከያ ሲሆን ኅብረተሰቡም በዚህ ልክ ተረድቶ ልጆቹን ማስከተብ እንዳበት ተናግረዋል፤ ለዚህም ግንዛቤን በመፍጠር እና ክትባቱ ተደራሽ እንዲሆን ብዙኃን መገናኛዎች ድርሻቸው የጎላ ነው። የሃይማኖት ተቋማትም በተመሳሳይ። በመሆኑም የሚመለከታቸው ሁሉ የድርሻቸውን እንዲወጡ ነው የጠየቁት።

የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በላይ በዛብህ እንዳስታወቁት በደቡብ ጎንደር ዞን እና ጎንደር ከተማ አስተዳደር በሽታው ተገኝቷል። በመሆኑም በዘመቻ ክትባቱን መስጠት አስፈላጊ ሆኗል።

በምሥራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ጎጃም እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች፣ በባሕር ዳር፣ በደብረ ታቦር እና በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደሮች ክትባቱ ይሰጣል። ከሦስት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ክትባቱን ይወስዳሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

ክትባቱ ከዐሥር ዓመት በታች ለሆኑ ሕጻናት ይሰጣል፤ በዚህ የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሕጻናት ከዚህ በፊት ቢከተቡም ባይከተቡም ክትባቱን መውሰድ እንዳባቸው አቶ በላይ ተናግረዋል።

የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ እንደ ሀገር በስድስት ክልሎች እና 22 ዞኖች የሚካሄድ ሲሆን በዚህም ስምንት ነጥብ አንድ ሚሊዮን ሕጻናት ተደራሽ ይሆና ተብሎ ይጠበቃል።

ወባ፣ የእብድ ውሻ በሽታ፣ ኩፍኝ፣ አጣዳፊ የምግብ እጥረት፣ አባ ሰንጋ፣ ፖሊዮ እና ኮሌራ በክልሉ ያሉ ዋና ዋና የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች (በሽታዎች) ስለመሆናቸው ከሰሞኑ የፖሊ ክባት ዘመቻን በተመለከተ በነበረ የባለድርሻዎች ምክክር ተነስቷል።

በምክክሩ እንደተነሳው ባለፉት ስምንት ወራት እንደ ሀገር በስድስት ክልሎች ወረርሽኙ ተከስቶ 40 ሕጻናት ተገኝቶባቸዋል። በርካት ሕጻናት አለመከተባቸው ለወረርሽኙ መዛመት ምክንያት ነው ተብሏል፡፡

 

(ጌትሽ ኃይሌ)

በኲር የጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here