“ሠንደቅ ዓላማ የሉዓላዊነታችን መገለጫ ነው”

0
26

18ኛው ሀገር አቀፍ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ጥቅምት 03 ቀን 2018 ዓ.ም ተከብሮ ውሏል፤ በዓሉ ‘’ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ከፍታ፤ ለብሔራዊ አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና ሕዳሴ’’ በሚል መሪ መልዕክት  ነው የተከበረው።

የአማራ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አማረ ሰጤ በዓሉን የማክበር ዓላማው ሠንደቅ ዓላማ ለብሔራዊ አንድነት እና ሉዓላዊነት ያለውን መገለጫነት ለማስገንዘብ ስለመሆኑ ጠቁመዋል። “ሠንደቅ ዓላማ የነጻነት እና የሉዓላዊነታችን መገለጫ ነው” ብለዋል።

አቶ አማረ እንዳሉት የሕዳሴ ግድብን ጨምሮ የተመዘገቡ ስኬቶችን መዘከር፤  ይፋ በተደረጉ አዳዲስ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ዙሪያ እና በሎሎችም ውይይት ማድረግ የበዓሉ አካል ናቸው።

ሠንደቅ ዓላማ ከቀደምት አባቶቻችን ጀምሮ የአርበኝነት እና የተጋድሏችን ምልክት ነው፤ የነጻነት እና የሉዓላዊነታችን መገለጫም ነው፤ እንደ ዓድዋ ባሉ ብሔራዊ ድሎችም ሠንደቅ ዓላማ የብሔራዊነት እና አንድነት መገለጫ ሆኖ አገልግሏል፤ የበዓሉ አከባበርም ለሠንደቅ ዓላማ ክብር የተከፈለውን መስዋዕትነት በሚያስታውስ መልኩ ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በአዋጅ መደንገጉን የጠቀሱት ምክትል አፈ ጉባኤው በየዓመቱ ጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ላይ እንደሚከበርም አንስተዋል።

 

(ዋሴ ባየ)

በኲር የጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here