ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
11

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካኝነት  ለግብርና ጽ/ቤት በክልሉ ምክር ቤት ጸድቆ ቤቴን በራሴ እገነባለሁ በሚል መርህ የገበሬ ማሰልጠኛ ተቋም በአርሶ አደር ሀብት በማሰባሰብ ይገንባ ተብሎ በተሰጠን አቅጣጫ መሰረት በጃንጓ ቀበሌ የጠበቀ የገበሬ ማሰልጠኛ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከደረጃ 6 (ስድስት) እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸዉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ከረዳት ገ/ያዥ ቢሮ ቁጥር 8 ከጥቅምት 10/2018 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 30/2018 ዓ/ም ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የግንባታዉን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ በፖስታዉ ታሽጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  7. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን በ22ኛው ቀን በተከታታይ ቀናት እስከ ህዳር 01/2018 ዓ/ም 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ህዳር 01/2018 ዓ/ም በ22ኛው ቀን 3፡30 ተዘግቶ በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በዚሁ ቀን በ4፡00 ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟላት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በሌሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ የመክፍት ስልጣን አለዉ፡፡
  10. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  11. ማንኛዉም ተጫራች /ተወዳዳሪ/ አሸናፊነቱ ተገልጾለት ዉል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ግንባታዉን በፍጥነት ሰርቶ የሚያስረክብ መሆን አለበት፡፡
  12. ጨረታዉ የሚከፈተዉ ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ በሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 335 06 01 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከተዉም፡፡

የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here