ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
22

የባሕር ዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2018 በጀት አመት በኮሌጁ ስታንድረዱን የጠበቀ የመዝናኛ ክበብ ግንባታ እንዲሰራ ይፈለጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የመዝናኛ ክበብ ግንባታዉ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ይህን የግንባታ ጨረታ የምትወዳደሩ ተጫራቾች ከደረጃ 1-7 ደረጃ ያላችሁ መሆኑን አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግዥ ንብ/አስ/ደ/የስራ በሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 05 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ 15 (ለአስራ አምስት) ለተከታታይ የሥራ ቀናት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚወዳዳሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ባሕር ዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 16ተኛዉ ቀን 2፡15 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዚሁ እለት 2፡30 ታሽጎ በዚሁ እለት 3፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም፡፡ የመክፈቻው ቀን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 058 220 07 71 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. ኮሌጁ ከፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል 100 ሜትር ገባ ብሎ ከኦክስጅን ማቀነባበሪያ ጎን ይገኛል፡፡

የባሕር ዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here