ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
18

በምሥራቅ ጎጃም ዞን በግንደወይን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የመኪና መለዋወጫ ስፒር ፓርት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለማሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሰዉን እና የሚመለከተውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሎት 1 ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት የጨረታ ሰነዱን ከመ/ቤታችን ረዳት ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር ለሎት 1 ብር 100,000/አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዛ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዝብ ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጀዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማለትም ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግንደወይን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 12 በ16 ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች በጨረታው ያወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን የማይወስድ መሆኑ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. አሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፈባቸውን እቃዎች ከተማ አስተዳደሩ ድረስ በራሱ ትራንስፓርት ወጭ ማቅረብ አለበት ፡፡
  13. መ/ቤቱ ጨረታ አሸናፊውን በጥቅል ዋጋ ይለያል፡፡
  14. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ አቤቱታ /ቅሬታ ካላቸው በተከታታይ 5 የሥራ ቀናት ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውጭ የመጣ ቅሬታ ጽ/ቤቱ የማይቀበል መሆኑን እን፡፡
  15. መ/ቤቱ ከአሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፋቸውን እቃዎች 20 በመቶ ከውል በፊት የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ እቃዎች በባለሙያ እየተረጋገጡ ርክክብ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
  16. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  17. አሸናፊው ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ከ5 የሥራ ቀናት በኃላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ መጥቶ ውል በመያዝ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  18. ከአሸናፊው ድርጅት 3 በመቶ የቅድመ ግብር የሚቆረጥ ይሆናል፡፡
  19. ግዥ ፈፃሚው አካል ግዥውን ለመገምገም፣ ለማፅደቅ፣ አቤቱታ ቢነሳ ለማስተናገድ እና አሸናፊ ድርጅቱ ጋር ውል እስገሚገባ ድረስ የመጫረቻ ሰነዱ ጸንቶ የሚቆየበት ለ40 ቀን ይሆናል፡፡
  20. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ በቁጥር 058 861 26 15 በመደወል ዝርዝር መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡

የግንደወይን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here