ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
23

የእብናት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለእብናት ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል ለ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ከእብናት እስከ እባጭኮ ቀበሌ 20 ኪሎ ሜትር  እና ከእብናት ዋሪባ ቀበሌ 20.4 ኪ/ሜ የመንገድ ጥገና ስራ ለማሰራት እና ከመጭና  እስከ ጉናኑና 10 ኪሎ ሜትር መንገድ  በአዲስ የቆረጣ እና ድልዳሎ ስራ  ለማሰራት የተለያዩ የማሽን ኪራይ ለማጫረት ይፈለጋል ፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ሁሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  4. የባለቤትነት ሊብሬ እና ኢንሹራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ከተራ ቁጥር 1-4 የተዘረዘሩትን ያላሟላ ተወዳዳሪ ከጨረታ ዉጭ ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጠቅላላ ዋጋ ድምር 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በእብናት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሥም በማሰራት ወይም በጥሬ ገንዘብ እብናት ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ዋና ገ/ያዥ ገቢ በማድረግ ገቢ የሆነበትን የገቢ ደረሰኝ ከኦርጅናል የጨረታ ሰነዱ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርጎ ኦርጅናል ሰነድ እብናት ወረዳ ገ/ጽ/ቤት/ግዥና/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 ባዘጋጀዉ ሳጥን ማስገባት ይችላል፡፡ ጨረታዉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ ለ21 ቀን ቆይቶ በ22ኛው ቀን ይከፈታል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ቢገኙም ባይገኙም በግዥና/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 ጨረታው በወጣ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
  9. አሸናፊው ለስራ በተፈለገበት ወቅት ለ3 ቀናት ተጠብቆ ካልቀረበ በመመሪያ መሰረት መ/ቤቱ እርምጃ ለመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝር በሚሞሉበት ወቅት ሥርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የጠፋ ከሆነ ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ፡፡
  11. የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 08 የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  12. ደረቅ ቸክ ማስያዝ አይቻልም፡፡
  13. አሸናፊው አሸናፊነቱን እንደተገለፀለት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እብናት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  15. ጨረታዉ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 20 ቀን ይሆናል፡፡
  16. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 440 06 06 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእብናት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here