በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የባንጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 1.1 የፕሪንተር ቀለም፣ ሎት 1.2 ሌሎች አላቂ እቃዎች፣ ሎት 1.3 የጽዳት እቃ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣ ሎት 3 ቋሚ እቃ ጀነሬተር እንዲሁም ሎት 4 የመኪና ጎማ ከነ ካላማዳሪው ከመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ የዋጋውን ጠቅላላ 10 በመቶ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች የንግድ ፈቃዳቸው በሚጋብዛቸው ብቻ መወዳደር አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ባንጃ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢን ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ሎት በየሎቱ ለእያንዳንዱ ብር 8,000 /ስምንት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንጃ ወረዳ ገ/ኢል/ጽ/ቤት ደረሰኝ በመሂ/1 ኮፒ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ፖስታ በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በባንጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 16 ተኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባችሁ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ16 ተኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ይታሸጋል፡፡ በዚሁ ቀን በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ የምንለየው ጥራቱን የጠበቀ እቃ ካቀረቡት ውስጥ በየሎቱ በጠቅላላ ድምር በዝቅተኛ ዋጋ የሞላውን ነው፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፏቸውን እቃዎች ባንጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ወጭ በባለሙያ እያስፈተሸ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
- ስለ ጨረታ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ባ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ግ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 227 06 47 /058 227 00 09 መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የባንጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት እንደ ሴክተር መ/ቤቶች በጀት አቅም 20 በመቶ የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ይከፈታል፡፡
የባንጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት