ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
13

በሰሜን ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የአዴት ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት ለአዴት ከተማ አስተዳደር ለመንግስት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሳሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥዉ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-3 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. የእቃዉን ዝርዝር መገለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን ወጥቶ ይቆያል ሰነዱን በአዴት ከተማ አስተዳደር ገን/ጽ/ቤት በግዥ ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 19 በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2 በመቶ ለሚወዳደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ በባንክ በተረጋገጠት (ቢድ ቦንድ) ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመ/ቤችን ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድረግ የገቢ ሰነድን ኮፒ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. የዋጋ መሙያ ፎርሙን በመሙላት በፖስታ በማሸግ በአዴት ከተማ አስ/ገን/ ጽ/ቤት በግዥና ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 19 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ16 ተኛው ቀን እስከ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በ16ኛው ቀን 3፡00 ላይ ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል፤ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ ቢኖረውና ለመለየት አስቸጋሪ ከሆነ ተጫራቹ ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
  11. አሸናፊው የሚለየው በእያንዳንዱ እቃ ዝርዝር በጠቅላላ ድምር በሎት ይሆናል፤ ዋጋ ነጣጥሎ መሙላት አይቻልም፡፡
  12. የሚገዙ እቃዎች ጥራታቸዉ የተጠበቀ መሆኑ በጥራት አረጋጋጭ ኮሚቴ /ባለሙያ/ ተረጋግጦ የምንረከብ መሆኑንና ልዮ ሙያ የሚጠይቅ ከሆነ በቴክኒካል ባለሙያዎች የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡
  13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 338 00 43 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  15. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለዉ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

ማሣሰቢያ፡- እኛ ከሸጥንላችሁ ሰነድ ውጭ በራሣችሁ ቅጽ መሙላት፣ በፍሉድ ማጥፋት፣ ሥርዝ ድልዝ፣ በራስ ስፔስፊኬሽን ዋጋ መሙላት፣ ዋጋ ነጣጥሎ መሙላት እና የድርጅት ማህተም ያላደረገ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡

የአዴት ከተማ አስ/ገ/አካ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here