ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
19

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ የጽዳት እቃዎችን፣ የተለያዩ የቋሚነት ባህሪ ያላቸው እቃዎችን፣ ፈርኒቸሮችን፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፣ Antivirous አጀንዳዎችን፣ የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎችንና ማስዋቢያዎችን፣ የብስክሌት ጎማ እንዲሁም የደንብ ልብሶችን በግልጽ ጨረታ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ድርጅቶች፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ እንዲሁም የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ  የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ማቅረቢያ በፖስታ በማሸግ እና ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ገንዘብ ቢሮ ባሕር ዳር ቢሮ ቁጥር 108 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል  ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱን በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይል፡፡ በ16 ተኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ይዘጋና በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባሕር ዳር ከተማ በሚገኘው አብክመ ገንዘብ ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ይከፈታል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋበት 16ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል፡፡ የመጫረቻ ሰነዱ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ ለቢሯችን ቢደርስ የጨረታ ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  6. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ (አገልግሎት) አይነት አብክመ ገንዘብ ቢሮ ድረስ እቃውን (አገልግሎቱን) ማቅረብ መስጠት ይኖርበታል፡፡
  7. ለእቃዎቹ የቀረቡት ስፔሲፊኬሽኖች፣ መመሪያዎችና የውል ቃሎች ከጨረታው ሰነድ ጋር በአባሪ የቀረቡ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  8. ጨረታው የሚዘጋጅበት ቋንቋ አማርኛ ይሆናል፡፡
  9. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ አብክመ ገንዘብ ቢሮ ቁጥር 108 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 13 56 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here