በደቡብ ጎንደር ዞን አዲስ ዘመን ከተማ የሚገኘው ርብ ኃላ/የተወሠነ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን ቀበሌ 04 በመደበኛ በጀት ለጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል ባለቢዝመንት ሦስተኛ ፎቅ (B+G+3) ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለሲሚንቶ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈረቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- አቅራቢዎች ህጋዊና በዘመኑ የታደሠ የንግድ የስራ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የወጣው ጨረታ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ዋጋ እንደሚሆን ሲገመት የተጨማሪ የእሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርበቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖረባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀረቡት የመጫረቻ ሰነድ በአማረኛ ቋንቋ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች በሚሞሉበት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸው እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በአዲስ ዘመን ከተማ ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ለ10 ተከታታይ ቀናት የመጫረቻ ሠነዱን ዋናው ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት በአካል (በህጋዊ ወኪላቸው) በኩል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ መዝጊያው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- የሲሚንቶ የሚቅረቢያ ቦታ አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላል፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን 10 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱ በ11ኛ ቀን ከረፋዱ 5፡30 ተዘግቶ በዕለቱ 6፡00 ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎች) በተገኙበት ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታው ሰነዱ በአንድ በጥንቃቂ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን የጨረታ ማስከበሪያውን ከኦሪጅናል ሰነዱ ፖስታ ውሥጥ በማደረግ መቅረብ አለበት፡፡
- ዩኒዬኑ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የሲሚንቶ አቀራረብ ሁኔታ በተመለከተ በተጫራቾች መመሪያ ይመልከቱ፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮችን በስልክ ቁጥር 058 444 00 61 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ርብ ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ስራ ማኅበራት ገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን


