በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የጣቁሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳዉ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉል ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡- በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት እንድትሳተፉ ይጋበዛል፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ በዘርፋ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
- የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ሻት) ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ጣቁሳ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ትብብር ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለተከታታይ 15 ቀናት 11፡30 ተሽጦ በ15 ተኛው ቀን 3፡30 ይታሸጋል፡፡
- ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣ በ16 ተኛው ቀን በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ጣቁሳ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ጽ/ቤት ይከፈታል፤ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታዉ አይስተጓጎልም፡፡
- ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፈው የሚለየው በሎት (በጥቅል) ዋጋ ነዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2 በመቶ ጥሬ ገንዘብ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊዉ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ዉስጥ ዉል መያዝ አለበት፤ የአሸነፈዉን ንብረትም ጣቁሳ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ትብብር ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ አምጥቶ ማስረከብ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 336 04 48 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጣቁሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


