ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
15

የጨረታ ቁጥር 008/18

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በ2ዐ18 በጀት አመት 1ኛ. የዳኞች ካባ ፣2ኛ. በዲስከን አንግል ብረት የሚሰራ የመዝገብ መደርደሪያ ሸልፍ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 / ሁለት መቶ ሽህ / እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ.1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጫራታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ግዥ እና ንብረት አስተዳዳር ቡድን በቢሮው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ህዳር 01 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ 15 ቀን በጋዜጣ ታትሞ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ህዳር 02 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሶስተኛ ፎቅ ግዥ ቡድን ይከፈታል፡፡ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 02 56 65 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here