ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
20

በደቡብ ጎንደር አስተዳዳር ዞን የፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ  መስሪያ ቤቶች ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የቢሮ መገልገያ እቃዎች፣ ሎት 3 የጽዳት እቃ፣ ሎት 4 የኤሌክትሮንክስ እቃዎች፣ ሎት 5 ፈርኒቸር፣ ሎት 6 የመኪና ጎማ እና ሎት 7 የስፖርት ትጥቅ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ይህ ግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ተኛው ቀን ድረስ በፋርጣ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በመምጣት ከዋናው ጋር ሊገናዘብ የሚችል ፎቶ ኮፒ ማስረጃ በማቅረብ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የጽህፈት መሳሪያ ብር 20,000 /ሃያ ሽህ ብር/ የቢሮ መገልገያ እቃዎች እና ለጽዳት እቃዎች ለእያንዳንዳቸው ብር 5,000 /አምስት ሽህ ብር/ ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ብር 20,000 /ሃያ ሽህ ብር/ ለፈርኒቸር ብር 5,000 /አምስት ሽህ ብር/ ለመኪና ጎማ 15,000 /አስራ አምስት ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (በጥሬ ገንዘብ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች በባንክ ያስያዙትን ገንዘብ ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ ከመ/ቤታችን ገቢ ያደረጉበትን የገቢ ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ አሽገው ፋርጣ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት ብለው በዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ቢሮ ቁጥር 5 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን የሚታሸገውም በዚሁ ሰዓት ነው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ተኛው ቀን በ3፡30 ድረስ ማስገባት የሚችል ሲሆን  በዚሁ ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ወይም ባይገኙም በግዥና  ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5  ይከፈታል፡፡
  9. የጨረታ መከፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊው የሚሆነው በጥቅል (በሎት) ወይም በተናጠል ሊሆን ይችላል፡፡
  11. እቃዎቹ የሚቀርቡት ፋርጣ ወረዳ አስተዳደር በየፑል ንብረት ክፍሎች /መጋዝን/ ይሆናል፡፡
  12. የሚገዙትን ዕቃዎች (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. የሚቀርቡት እቃዎች በባለሙያ ተረጋግጠው የሚገቡ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጡ ዝቅተኛ ስፔስፊኬሽን ያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 441 30 36 ደውለው ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here