የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2018 በጀት አመት በዞኑ ሥር ለሚገኙት መምሪያዎች አገልግሎት የሚውል 1. ሎት የጽህፈት መሳሪያ እና ሌሎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃ፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 4 ፈርኒቸር እቃዎችን በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባው፡-
- የግብር ከፋይ የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ አግባብ ያለው የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱትን የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ መሂ 1 በማስያዝ ጨረታው እስከ ሚዘጋበት ሰዓት ድረስ ግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ውስጥ ወይም ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤ ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም፤ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም የሚያስይዙት ዋስትና ከአንድ በመቶ ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቹ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር በማያያዝ በፖስታ ውስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ የተሞላበት ሳይኖረው ኦርጂናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ የሚቆይበት ጊዜ ጥቅምት 17/2018 እስከ ህዳር 01/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ህዳር 2/2018 ዓ.ም በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 የከፈታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊ የሆነበትን እቃዎች የሚያቀርበው ለሰ/ጎ/ዞን ንብረት ክፍል የሚያስረክብ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፤ የጨረታ ውድድር የሚካሄደው በሎት ወይም በነጠላ ዋጋ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ የሚወስድ ይሆናል፡፡
- የጨረታው መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- መስሪያ ቤቱ ይህንን ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 1 ዘወትር በስራ ሰዓት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 058 417 25 44 /058 417 01 26 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ

