ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
32

የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት የ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን ማለትም ሎት 01 ደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ፣ ሎት 02 ደንብ ልብስ የተዘጋጁ፣ ሎት 03 ደንብ ልብስ ጫማ፣ ሎት 04 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 05 ህትመት፣ ሎት 06 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 07 ልዩ ልዩ መገልገያ፣ ሎት 08 የኤሌክተሮኒክስ እቃዎች እና ሎት 9 የመኪና እስፔር ፓርት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባቸው፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና አግባብነት ያላቸው የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱት የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙት የእቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፤ ከተጠቀሰው ስፔስፊኬሽን ውጭ ሰርዞ ሌላ ማስገባት ከውድድሩ ውጭ ያደርጋል፡፡
  6. የጨረታ ማስታወቂያዉን ጥቅምት 17/2018 በሚወጣዉ በጋዜጣ መመልከት ወይም ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሰሜን ጎንደር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 15 ብር 30 /ሰላሳ ብር/ በመግዛት መዉሰድ ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ ከተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በመ/ቤታችን ዋና ገ/ያዥ በመሂ1 በመቁረጥ ጨረታው እስከ ሚዘጋበት ድረስ ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤ ይሁን እንጅ በጥሬ ገንዘብ ማስገባት አይቻልም፤ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም ያስያዙት (ሲፒኦ) ከአንድ በመቶ ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖረው ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ መስሪያ ቤታችን ባዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  10. ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ በጋዜጣ ከወጣበት ከጥቅምት 17/2018 ዓ/ም እስከ ህዳር 1/2018 ዓ/ም ጀምሮ የሚቆጠር ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱ ይሸጣል፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰ/ጎ/ዞ/ከፍ/ፍቤት ህዳር 2/2018 ዓ/ም ከረፋዱ በ4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡
  12. አሸናፊው እቃዎቹን ሰሜን ጎንደር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ንብረት ክፍል በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  13. የግዥ መጠን ከብር 20,000 /ሃያ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ 3 በመቶ ታክስ መክፈል አለበት፡፡
  14. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሀሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡ የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሎት ወይም በነጠላ በሞላው ዋጋ ሲሆን ተጫራቾች ሁሉንም ዝርዝር ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡ ያልሞላ ተጫራቾች ቢኖር ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  15. የጨረታ መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም መሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  16. አሸናፊው ተጫራች የእቃዎችን ጥራት በተመለከተ ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች ጥራቱን በማረጋገጥ ማስረከብ ግዴታው ነው፤ በጥራት አረጋጋጭ ባለሙያ መሰረት የጥራት ችግር ያለባቸውን ሙሉ በሙሉ በመመለስ ትክክለኛ ጥራት ያላቸውን እቃዎች የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  17. መ/ቤቱ ጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስልክ ቁጥር 09 42 04 69 78 /09 18 09 85 86 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here