በደቡብ ጎንንደር ዞን የሃሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሀሙሲት ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉል በምድብ 1 የደንብ ልብስ፣ በምድብ 2 የእስቴሽነሪ እቃዎችን፣ በምድብ 3 ሌሎች አላቂ የቢሮ እቃዎችን ፣በምድብ 4 ህትመት ፣በምድብ 5 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ፣በምድብ 6 የፈርኒቸር እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ፡-
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ከብር 200,000 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የእቃዎችን ዝርዝሩ መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከረዳት ገንዘብ ያዥ ክፍል ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ናሙናዎቹን ከዚሁ ክፍል ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለዉድድር ያስቀመጡትን ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብቻ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ያስያዙትንም (ሲፒኦ) ወይም የገቢ ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡንና ማስረጃዎችን ዋናዉን በጥንቃቄ በታሸገ በአንድ ፖስታ ለሃሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን ተብሎ ተጽፎበት ቢሮ ቁጥር 4 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 16ኛዉ ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ የሚታሽገውም በዚሁ ሰዓት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በገንዘብ ጽ/ቤት በ16ኛዉ ቀን 4፡00 በጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊዉ ማሸነፉ ከተገለጸለት ከ5 ቀናት በኋላ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ዉስጥ ገንዘብ ጽ/ቤት ቀርቦ ባሸነፈበት ገንዘብ መጠን ልክ የዉል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ዉል መዉሰድ ያለበት ሲሆን በወቅቱ ቀርቦ ዉል ካልወሰደ በግዥ መመሪያዉ መሰረት አስፈላጊዉን እርምጃ ይወሰዳል፡፡
- የሚቀርቡ አቅርቦቶች የሚያቀርበዉና ርክክብ የሚፈጸመዉ ጥራቱ ከተረጋገጠ በኋላ በሃሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ሃሙሲት ከተማ ላይ ይሆናል፡፡
- የጨረታ መክፈቻዉ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከናወናል፡፡
- የጨረታ አሸናፊዉ የሚለየዉ ለሁሉም ዕቃዎች በሰጠዉ ጥቅል ዋጋ ድምር የሚወስን ሲሆን በሰነዱ የዋጋ መሙያ ቦታ ላይ የአንዱንም እቃ ዋጋ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ስለጨረታዉ ዘርዝር መረጃና ማብራሪያ ከፈለጉ ሃሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 443 03 20 /04 00 /09 18 53 10 53 ደዉለዉ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ ፡፡
የሃሙሲት ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት

