ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
12

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር የሻሁራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሣሪያ እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የሚገዛው የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር /በላይ ከለሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን እና የቫት ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ድምር 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒ.ኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በበተቋሙ የገቢ ደረሰኝ መሂ-1 ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና ማስረጃዎችን ማለትም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ሠርተፊኬት፣ ቫት ሰርተፊኬት የማይመለስ ፎቶ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ ከጨረታ ሰነዱ ፖስታ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ ከወጣበት ከጥቅምት 24/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 09/2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ከሻሁራ ከተማ አስተዳደር ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ በማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. የሁሉም የእቃ ዓይነቶች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ ከሻሁራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ን/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ከጥቅምት 24/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 09/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሳጥኑ ከሚታሸግበት የመጨረሻ ሰዓት እና ደቂቃ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከሻሁራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን በዓል ወይም እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ካልተገኙ የጨረታ ሰነዱ እንዲከፈት ተደርጎ  ያልተገኙ ተጫራቾች ግን በእለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ማንኛዉንም የመንግስት ግብር፣ የትራንስፖርት ወጭና ሌሎች ወጭዎች ካሉ ማካተት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ተጫራቾች የአሸነፉትን እቃ ከሻሁራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሳቸው ወጭ በማምጣትና በባለሙያና በጥራት አረጋጋጭ ኮሚቴዎች በማስፈተሽ ወይም በማስመርመር የማስረከብ ግዴታ አለባቸዉ፡፡
  12. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት የተከለከለ ነው፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የሻሁራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here