- የጨረታ ዙር 1ኛ /2018 ዓ.ም
- የጨረታዉ ዓይነት /መደበኛ
- የሻሁራ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገዉ አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረዉ መሰረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ማለትም መኖሪያ፣ ድብልቅ እና ንግድ መጋዝን የተዘጋጀ ቦታን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛዉም አካል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከጥቅምት 24/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 3/2018 ዓ/ም የቦታዉን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ሻሁራ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 27 ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከ ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የህዳር 3/2018 ዓ/ም ይሆናል፡፡
- ጨረታዉ የሚዘጋዉ ህዳር 3/2018 ዓ/ም ከቀኑ በ11፡00 ይሆናል፡፡
- ቦታዉን መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ጥቅምት 25፣27 እና 28 /2018 ዓ.ም የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
- ጨረታዉ የሚከፈተዉ ህዳር 4/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 በሻሁራ ከተማ አስተዳደር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይሆናል፡፡
- ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ በሥልክ ቁጥር 09 18 18 40 99 /09 18 71 22 20 /09 36 18 77 11 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ጨረታዉን የማራዘም እና ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
የሻሁራ ከተማ አስ/ከተ/መሰ/ልማት ጽ/ቤት

