የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የጽዳት እቃዎች እና ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መ/ቤቱ ባወጣው ግልጽ ጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡
- የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅርብ የሚችሉ፡፡
- የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅርብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ኮፒውን እና የዋጋ መሙያቸውን ኦርጅናል በአንድ ፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የሰነዱን ዝርዝር መግለጫ ከደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በመምጣት ከዋና ገ/ያዥ ብር 50 /አምሳ ብር/ ብቻ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጨማሪ ማስረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 12 05 79 24 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይም ጠቅላላ ዋጋ 0.5 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታው ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሃሣቡን በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ወጥቶ ይቆያል ጨረታው የሚከፈትበት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው ቀን 3፡30 ታሽጐ ጨረታው የሚከፈተው በዕለቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ከጠቅላላ ዋጋው ውስጥ 10 በመቶ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚሰጧቸውን የመጫረቻ ዋጋዎች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ያልተመሰረቱ መሆን አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ ከተጠቀሱት እቃዎች ተጫራቹ የሞላውን ዋጋ ሳይለውጥ 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- 14 አሸናፊው ድርጅት የአሸነፋቸውን እቃዎች ደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ግዥው በሎት የሚፈፀም የሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤት

