በአፈ/ከሳሽ አቶ ስሜነህ መኮነን እና በአፈ/ተከሳሽ አቶ ጌትነት ዳኛው መካከል ስላለው የገንዘብ አፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በግምጃ ቤት ከተማ ቀበሌ 02 የሚገኝ፤ በምሥራቅ በደቡብ እና በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን ክፍት ቦታ ተዋስኖ የሚገኘው የተከሳሽ ንብረት የሆነ የድርጅት ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 1‚569‚000 (አንድ ሚሊዩን አምስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሽህ ብር) ስለሚሸጥ፤ መጫረት የምትፈልጉ ጨረታው ከጥቅምት 24/2018 እስከ ህዳር 24/2018 ዓ/ም በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ፤ ህዳር 25/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 – 5፡00 የመነሻ ዋጋውን ¼ኛውን በባንክ በስፒኦ በማስያዝ መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባንጃ ወ/ፍ/ቤት

