ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
22

ቁጥር 07/2018

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ሎት1. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት2. የፈርኒቸር ዕቃዎችን ፣ሎት3. የልጆች ቻናል ስቱዲዩ የኢንቴረር ስራን ደረጃ 8 የማጠናቀቅ (የማስዋብ) ሥራ ፈቃድ ካለቸዉ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ ዘዴ ተጯራቾችን አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የከተማ ልማት የብቃት የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፍኬት፡ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሎት1. እና ሎት2. በተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀን እንዲሁም ለሎት3. በተከታታይ 21 /ሃያ አንድ/ ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ 500 /አምስት መቶ/ ብር በመግዛት፤ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 106 መዉሰድ ይቻላል፡፡ የሎት1. የቴክኒክ እና የፋይናስ ሰነዶችን ለየብቻ በመሙላት፣ ሎት2. እና ሎት.3 የፋይናንስ ኦርጂናልና ኮፒ ሰነዶችን በሁለት ኮፒ በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት ለዚህ ሲባል በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን ሎት1. እና ሎት2. በ16ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ ፡፡ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በቴክኒክ ምዘና 70 እና በላይ ነጥብ  ያመጡ ድርጅቶች ወደ ፋይናንስ ዉድድር የሚቀርቡ ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው ሎት 1.እና ሎት2. በ16ኛው ቀን ሎት3. በ22ኛዉ ቀን ከቀኑ 4፡00  ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ (ስፒኦ) ፣በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈተው ለሎት1. እና ሎት2. በ16ኛው ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል እንዲሁም ለሎት3. በ22ኛዉ 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል ቀኑ በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30  ይከፈታል፡፡
  7. ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የሚፈለጉትን የኤሌክትሮኒክስ ፣የፈርኒቸር ዕቃዎች እና የልጆች ቻናል ኢንቴረር ስራ ዓይነት፣ ብዛትና ስፔስፍኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 ድረስ በመምጣት መግዛት ይቻላል፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here