ወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አገልጋሎት የሚውሉ ሎት 1 መድሃኒት፣ ሎት 2 ሬጀንት፣ ሎት 3 የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች፣ ሎት 4 የተሸከርካሪ ጎማና ባትሪ እና ሎት 5 የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ፡-
- ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላችሁ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- ንግድ ፈቃድና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ብር ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ከጨረታ ሰነዱና ከታሸገው ፖስታ ላይ የድርጅት ማህተም ተነባቢ በሆነ መልኩ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበት የእቃ ዋጋ ድምር ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ 3 በመቶ ተቀንሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡ መ/ቤቱ ቫት በመመሪያው መሰረት ይሰበስባል፡፡
- ተጫራቾች የሞሉትን የዋጋ አንድ በመቶ በጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይም ከተፈቀደላቸው ባንክ በተመሰከረለት (ሲፒኦ) በማሲያዝ ከፖስታው ውስጥ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራችው በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታ እራስን ማግለል አይቻልም፡፡
- የጨረታ ሰነድን ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የአማራ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ያወጣውን ግዥ አፈጻጸም መመሪያ አዋጅ ቁጥር 1/2003 እና ተሻሽለው ለወጡ መመሪያዎችና አዋጆች ተገዥ መሆን ይገባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከጥቅምት 24/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 14/2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ተከታታይ ለ21 ቀናት በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በህዳር 14/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ የጨረታ ሳጥኑ በዚህ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመመሪያው መሰረት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ በሚከፈትበት ወቅት ባይገኙም በመመሪያው መሰረት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱም የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ መክፍቻ ቀን በዓል ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፋል፡፡
- አሸናፊው ማሸነፉ ተነግሮት ውል ከወሰደ በኋላ ሆስፒታሉ በሚያዘው መሰረት ገዝቶ ማቅረብ አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ውለታ ከወስደበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም ድረስ ሲታዘዝ ማቅረብ አለበት፡፡
- የተጠቀስውን እቃ በጨረታ አሸናፊው ወጭውን ችሎ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
- ከሎት 1፣ 2 እና ሎት 3 ውጭ ያለው ውድድሩ በሎት ድምር ነው፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስራ ሂደቱ ስልክ 033 331 01 72 እና 033 331 02 52 ደወሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

