በአፈ ከሳሽ የታዳጊዋ ተኩለሽ ገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበር እና በአፈጻጸም ተከሳሾች 1ኛ አቶ መሳይ በየነ እና 2ኛ አቶ ታደሰ ደስየ መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በታዳጊዋ ተኩለሽ ከተማ በአቶ ታደሰ ደስየ ስም የተመዘገበ በምዕራብ መንገድ በሰሜን አሻግሬ አድሱ፣ በደቡብ የእግር መንገድ እና በምሥራቅ ፈቃደ አሊጋዝ ተዋስኖ የሚገኝ 176.767 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ የቆርቆሮ ክዳን ቤት በጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 256,685.97 /ሁለት መቶ ሀምሳ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ሰማኒያ አምስት ብር ከዘጠና ሰባት ሳንቲም/ ሆኖ ህዳር 05 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 እስከ 6፡00 ድረስ በግልጽ ጨረታ ስለሚሸጥ መጫረት የሚፈልግ አካል ማንነቱን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ በሰዓቱ እና በቦታዉ በመገኘት ተመዝግቦ መጫረት የሚችል መሆኑን እና የመጨረሻ አሸናፊ ያሸነፈበትን 1/4 ኛዉን ወዲያውኑ በሞደል 85 ማስያዝ የሚጠበቅበት መሆኑ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የተኩለሽ ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት

