የሊዝ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
15

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8/1 መሰረት በ2018 በጀት አመት ለ1ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ ቤት ብዛት 34፤ ለድርጅት ብዛት 2 በድምሩ 36 ቦታዎችን በጨረታ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-

  1. መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 11፡30 ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 3 ማስገባት ይችላሉ፡፡
  3. ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በ3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ካልሆነም ተጫራቾች (ወኪሎቻቸው) ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 03 ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
  5. ይህ ማስታወቂያ ተግባራዊ የሚሆነው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡
  6. ሌሎች ተጨማሪ ዝርዝር ሃሳቦችን /ህጎችን/ ከሚሸጠው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  1. ስለጨረታው ዝርዝር መረጀ ከፈለጉ በጽ/ቤቱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ወይም በስልክ ቁጥር 058 445 01 92 ወይም 058 445 13 60 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here