ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
15

የመቄት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስተዳደር ቡድን ለመቄት ወረዳ ለሴክተር መሥሪያ ቤቶች መደበኛ በጀት እና መደበኛ ባልሆነ በጀት በሎት ጠቅላላ ድምር ማለትም፡- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 4 የመኪና ጐማና ባትሪ፣ ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 6 የውሃ መለዋወጫ እቃዎች እና አፍራዲፓምፕ፣ ሎት 7 የህንፃ መሳሪያዎች እና ሎት 8 የማሽነሪ ኪራይ ሲሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በሙሉ መወዳደር ትችላላችሁ ፡፡

  1. ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ተመዝጋቢ የሆኑ
  3. የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያላቸው፡፡
  4. በስማቸው የታተመ ደረሰኝ ያላቸው፡፡
  5. የግዥው መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ (በሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  7. የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ (በሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  8. በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ሥርዝ ድልዝ የሌለው መሆን ይኖርበታል፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በስም በታሸገ ፖስታ ማስገባት የሚችሉ፤ በስም የታሸገ ቢሆን ይመረጣል ባለመታሸጉ ጨረታውን ውድቅ አያደርገውም፡፡
  10. ጨረታው የሚቆየው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ሁል ጊዜ በሥራ ቀናት እስከ 11፡30 የጨረታ ሰነዱ ይሸጣል፡፡
  11. የጨረታ አሸናፊው ግለሰብ ወይም ድርጅት እቃውን ገቢ የሚያደርገው መቄት ወረዳ ባሉ ሴክተር መ/ቤቶች ንብረት ክፍል ይሆናሉ፡፡
  12. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጐ በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ የሚከፈት ይሆናል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በአል ወይም ከመንግስት የሥራ ቀን ውጭ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ስለዚህ መስፈረቱን የምታሟሉ ተጫራቾች የእቃውን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የምትችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን መቄት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 13 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  13. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ለበለጠ መረጃ በሥልክ ቁጥር 033 211 00 91 ወይም 033 211 00 90 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- የጨረታ ሰነዱ የሚገባዉ መቄት ወረዳ ግ/ን/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 13 በሚገኘዉ ሳጥን ዉስጥ ነዉ፡፡

የመቄት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here