ፀደይ ባንክ (ኢማ) እንጅባራ ቅርንጫፍ ለአቶ ወለላው በላይ እና ወ/ሮ ትዕግስት አበራ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን በሰንጠረዡ ከዚህ በታች የተገለፀ መኖሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሸሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
| የተበዳሪው ስም | የመያዣ ሰጭ ስም | የካርታ ቁጥር/የይዞታ መለያ ቁጥር | ቤቱ የሚገኝበት ቦታ | የቦታው ስፋት | የንብረቱ አይነትና አገልግሎት | የጨረታ መነሻ ዋጋ | የጨረታ ቀንና ሰዓት | ጨረታው | 
| ወለላው በላይና ትዕግስት አበራ | ወለላው በላይና ትዕግስት አበራ | AM010010504019 | እንጅባራ ከተማ 01 ቀበሌ | 200.875 ካ/ሜ | መኖሪያ ቤት | 3,417,192.49 | ህዳር 27/2018 ዓ.ም ከ3፡00 እስከ 6፡00 | ለመጀመሪያ ጊዜ | 
በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ኛውን በጥሬ ገንዘብ ወይም (ሲፒኦ) በፀደይ ባንክ ስም (አ/ማ) በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
 - በጨረታው የሚሳተፈው በሕግ ሰውነት ያገኘ ሰው ከሆነ የድርጅቱ መመሥረቻ ጽሑፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ፣ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ሕጋዊ ውክልና ማቅረብ አለበት፡፡
 - የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጡ ይሆናል፡፡
 - የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ አጠቃልሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ (በሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
 - በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት (ሲፒኦ) ይመለስላቸዋል፡፡
 - የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግሥት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈል ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጭዎች ይከፍላል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀረው የሊዝ ክፍያ ገዥው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል፡፡
 - ተጫራቾች ቤቱን በቀን ህዳር 26/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በባንኩ አማካኝነት መጎበኘት ወይም ማየት ይችላሉ፡፡
 - የጨረታው ቦታ በእንጅባራ ከተማ 01 ቀበሌ በሚገኘው የፀደይ ባንክ አ/ማ እንጅባራ ዲስትሪከት 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
 - ባንኩ ለሽያጭ ያቀረበዉን ንብረት የሚሸጠዉ በጥሬ ገንዘብ ወይም በከፊል ብድር ሲሆን አሸናፊ በባንኩ የብድር ፖሊሲ መሠረት አስፈላጊዉን መስፈርቶች ከአሟላ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል፡፡
 - ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 - ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 058 270 07 08 እና 09 10 30 20 03 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
 
ፀደይ ባንክ (ኢማ) እንጅባራ ቅርንጫፍ

