ቁጥር 143/ግ/ፋ/ን-3
በሰሜን/ጎጃም ዞን በመርዓዊ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ አካባቢ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ውስጥ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት2 ህትመት፣ ሎት 3. ኤሌክትሮኒክስ ፣ሎት4. ፈርኒቸር ፣ሎት 5. የፅዳት ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የሆነ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ
- የግዥ መጠኑ ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አይይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በፖስታ በማሸግና በሁሉም ሰነዶች ላይ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፣ሙሉ አድራሻ ፣ስልክ ቁጥር በማስፈር በዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚቀርቡ ዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መርዓዊ ከ/አስ/ገንዘብና አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስ ንብ አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 18 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 12,000 ብር/አስራ ሁለት ሽህ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ባለሙያ ማረጋገጫ የሚያስፈልጋቸው እቃዎች በባለሙያ ታይተው ገቢ የሚደረጉ ይሆናል ፡፡
- ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለጸ በኋላ የድርጅቱን ስም የሚጠቅስና ተከታታይ ቁጥር ያለዉ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው የሚያቀርበውን የእቃ አይነትና ጥራት ናሙና ቀድሞ የማሳየት ግዴታ አለበት፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን ህዳር 9/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጧቱ 4፡30 የሚከፈትና አሸናፊው የሚለይ ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሣጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ በሌሉበት ሠነዱ ተሟልቶ ከተገኘ ጫራታዉ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- በመ/ቤቱ የተሻለ ጥቅም አገኛለሁ ብሎ ካመነ አሸናፊውን በተናጠል ዋጋ ወይም በጠቅላላ ዋጋ የሚለይ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ከሚገዛቸው ዕቃዎች ላይ 20በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታ ማስታወቂያዉ ላይ ያልተጠቀሰ ነገር ቢኖር በግዥ መመሪያዉ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
- ለበለጠ መረጃ መርዓዊ ከ/አስተዳደር ገንዘብና አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በመርዓዊ ከተማ አስ/ገ/አካ/ኢኮ/ትብብር ጽ/ቤት

