ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
51

በሰሜን ጎጃም ዞን የይ/ዴ /ወ/ገ/ ኢ/ት/ ጽ/ቤት ለይ/ዴ/ወ/ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ቁሳቁሶች ማለትም ሎት1. የጽህፈት መሳሪያ እና ሎት2.የጽዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡                                         ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራች መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡

  1. የቲን ተመዝጋቢ መሆናቸዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. በዘርፉ አግባብ ያለዉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ማስረጃ ያላቸው፡፡
  3. ግዥው ከ200‚000 ብር (ሁለት መቶ ሽህ) ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ሂሳብ የጽህፈት መሳሪያ ብር 25‚000 /ሃያ አምስት ሺ / እና የጽዳት ዕቃ ብር 8‚000 /ስምንት ሺ/ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ከዋና ገንዘብ ያዥ አስይዘዉ ለግዥ ኦፊሰሮች ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከሆነ ከፖስታ ዉስጥ አስገብተዉ ማሸግ ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ካለ ከአሸናፊዉ ዋጋ ጋር ተደምሮ ሲያዝ የተሸነፈዉ ተጫራች የሚያስይዘዉ ገንዘብ ይመለስለታል፡፡
  6. ጨረታዉ የሚከፈትበት ዕለት በበዓል ቀናት ከሆነ ወደ ቀጣዩ የስራ ቀን ይሸጋገራል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን ከህዳር 1/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 15/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ታትሞ የሚቆይ ሲሆን የተሞላበትን ፎርም ቲን ፣ የንግድ ፈቃድዎንና ሌሎች ያልተጠቀሱ ማስረጃዎችን በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡
  8. ጨረታዉ የሚዘጋው ህዳር 16/2018 ዓ.ም በ3፡30 ሲሆን ጨረታዉ የሚከፈተዉ በተመሳሳይ ቀን በ4፡00 ቢሮ ቁጥር 3 ፍላጎት ያለዉ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በጨረታዉ መክፈቻ ዕለት ባይገኙ መ/ቤቱ ጨረታዉን ለመክፈት የሚገድበዉ የለም፡፡
  10. አሸናፊ አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ 10 በመቶ የዉል  ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መያዝ አለበት፡፡
  11. ተጫራቾች አሽገዉ ከሚያስገቡት ሰነድ እና ፖስታ ላይ አድራሻና የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡
  12. ተጫራቾቹ በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  13. ጨረታዉን የምናወዳድረዉ በሎት ወይም በጠቅላላ ዋጋ ነዉ፡፡
  14. ግዥ ፈጻሚ አካል ያሸነፈውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ እንዳስፈላጊነቱ 20በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  16. የሚሞላው ዋጋ ማንኛውንም ታክስ ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  17. ጨረታዉ ለ40 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፤ የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት 200 /ሁለት መቶ /ብር ብቻ ነዉ፡፡
  18. በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ ማስረጃ ቢያስፈልጋቸዉ የይ/ዴ/ወ/ገ/ኢ/ትብ/ጽ/ቤት ግዥ/ን/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ወይም በስልክ ቁጥር 058 338 02 98 ማግኘት ይችላሉ፡፡

የይልማና ዴንሳ ወ/ገ/ን ኢኮ/ት/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here