የአብክመ ፍትህ ቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያ እቃዎችን፣ የብስክሌት ጐማ ከነካላማዳሪው ፣ የመኪና ዲኮር፣ የመኪና ጐማ ከነካላማዳሪው፣ የሞተር ብስክሌት ጐማ ከነ ካላማዳሪው፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና የእጅ ዋጋ፣ የችሎት ካባ በሣምኘሉ መሰረት ሰፍቶ የሚያስረክብ፣ ፣ የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች ፣የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣የተለያዩ ፈርኒቸር ዕቃዎች ፣የተለያዩ ህትመቶች ፣አመታዊ የመኪና መለዋወጫ የሞተር ሳይክል ዕቃዎች የጄኔሬተር ዕቃዎች እና የቢሮ ብራንድ ህትመት በጥቅል ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ.1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ሲያቀርቡ የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 05 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል መውሰድ ይቻላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ሎት1. የጽህፈት መሣሪያ ዕቃዎች ብር 23,000 (ሃያ ሶስት ሺህ ብር) ፣ሎት6. የብስክሌት ጐማ ከነ ካላማዳሪው ብር 1,500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) ፣ሎት6. የመኪና ዲኮር ብር 8,000 (ስምንት ሺህ ብር) ሎት4. የመኪና ጐማ ከነካ ላማዳሪው ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ፣ሎት5. የሞተር ብስክሌት ጐማ ከነካላማዳሪው ፣ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) ሎት1ዐ. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና የእጅ ዋጋ፣ ብር 3,000 ( ሶስት ሺህ ብር)፣ ሎት13. የችሎት ካባ በሣምኘሉ መሰረት ሰፍቶ የሚያስረክብ ብር 3,000 (ሶስት ሺህ ብር)፣ ሎት 2. የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች ብር 7,000 (ሰባት ሺህ ብር)፣ ሎት 3. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 8,000 (ስምንት ሺህ ብር)፣ ሎት8. የተለያዩ ፈርኒቸር ዕቃዎች ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)፣ ሎት9. የተለያዩ ህትመቶች ብር 5,000.00( አምስት ሺህ ብር)፣ ሎት11. አመታዊ የመኪና መለዋወጫ፣ የሞተር ሳይክል ዕቃዎች የጄኔሬተር ዕቃዎች ብር 28,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)፣ ሎት12. የቢሮ ብራንድ ህትመት ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)፣ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ፍትህ ቢሮ ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማለትም ከህዳር1/2018 እስከ ህዳር 15/2018 ዓ/ም ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 04 በ16ኛው ቀን ህደር16/2018 ዓ.ም 3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ይከፈታል፤ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 31 00 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
አብክመ ፍትህ ቢሮ

