ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ        

0
44

ለእብናት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ህትመት እና ሎት 4 እድሳት እና ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ወይም ተቋሙን ማሳደስ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መወዳደር ለምትፈልጉ መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ግዥ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  4. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በእብናት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናሉን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርገው እብናት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተዘጋጀው የጨረታ  ሳጥን ውስጥ ማስገባት  አለባቸው፡፡
  7. ሆስፒታሉ የሚገዛቸውን እቃዎች ወይም እድሳት እና ጥገና 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
  8. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የቀረቡትን እቃዎች ወይም እድሳት እና ጥገና ዝርዝሩን ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው፤ አንድም እቃ አለመሙላት ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
  9. የሚገዙትን እቃዎች ወይም የእድሳት እና ጥገና አይነት (ስፔስፊኬሽን) መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡
  11. ሆስፒታሉ አሸናፊውን በጥቅል ዋጋ ይመርጣል፡፡
  12. ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ቢገኙም ባይገኙም በ16ኛው ቀን ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ በሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ በ8፡30 ይከፈታል፡፡
  13. አሸናፊው ድርጅት የአሸነፋቸውን እቃዎች እብናት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ የሚችል፡፡
  14. በሎት 4 ላይ የተጠቀሰው እድሳት እና ጥገና ተጫራቾች ሙሉ ማቴሪያሉን ራሳቸው በማቅረብ መስራት የሚችሉ እና ደረጃቸው ከደረጃ 7 በላይ መሆን አለበት፡፡
  15. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ተጫራቾች በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ስትሞሉ ሥርዝ ድልዝ (በፍሉድ) የጠፋ መኖር የለበትም
  17. አሸናፊው ተጫራች በስሙ የታተመ ህጋዊ ደረሰኝ ያለው መሆን አለበት፡፡
  18. ደረቅ ቸክ ማስያዝ አይቻልም፡፡
  19. አሸናፊው ተጫራቾች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኃላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ በማስያዝ ውል መውሰድ አለባቸው፡፡
  20. ጨረታው ከተዘጋ በኃላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  21. በተለያያ ምክንያት የጨረታ ሰነዱ ችግር ቢኖርበት ይህ ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስተካከያ የሚደረግበት ይሆናል፡፡
  22. ተጫራቾች ለማሸነፍ ሲባል የተወሰኑትን እቃዎች በጣም በዝቅተኛ ዋጋ ሞልቶ አላቀርብም (ገበያ ላይ የለም) ማለት አይቻልም፡፡
  23. በዚህ ሰነድ ያልተገለፀ ሀሳብ ቢኖር በግዥ መመሪያው መሰረት ተግባራዊ ይሆናል፡፡
  24. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 440 09 13 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእብናት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here