በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት በመደበኛ ካፒታል በጀት በሙሉ ዋጋ በጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ በደረጃ 9 /ዘጠኝ/ እና በላይ በጉንኮ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ በዳብር 1ኛ ደረጃ ት/ቤት እና በአንጅባ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የሥራ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የንግድ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለማሸነፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 ተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገነቡት ግንባታዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግንባታውን ጠቅላላ ዋጋ 1.5 መቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጽ/ቤቱ መሂ 1 በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከህዳር 01/2018 ዓ/ም እስከ ህዳር 21/2018 ዓ/ም ለተከታታይ 21 ቀናት በጋዜጣ ወጥቶ ይቆያል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ህዳር 22/2018 ዓ/ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በቀን ህዳር 22/2018 ዓ/ም በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 118 05 21 ወይም ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመገኘት ማብራሪያ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እና በተጨማሪም ልዩ ልዩ ማስረጃዎችን በተጫራቾች መመሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

