የሰሜን ወሎ ዞን ፍላቂት ገረገራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ቡድን ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶች ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ፣ ሎት 5 የመኪና መለዋወጫ እቃ፣ ሎት 6 የመኪና ጎማና ባትሪ በግልጽ ጨረታ በሎት ድምር አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾችን መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደስ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥ አገልግሎት መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዝጋቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናሉንና ኮፒ በሰም በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚገዙ እቃዎች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ እያንዳንዱ ሎት በማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ከገንዘብ ያዥ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የእቃውን የአገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ለፍ/ገ/ከ/አስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት ህጋዊ ደረሰኝ መሂ 1 ተቆርጦ ኮፒውን ወይም የጥቃቅን ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልግ ጨረታ የጥቃቅን ተጠቃሚ ከሆኑ ልዩ ድጋፍ ሰነዱ ጋር ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በጋዜጣ ወጥቶ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይታ ከህዳር 01/2018 ዓ/ም እስከ ህዳር 15/2018 ዓ/ም እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ሰነዱ ከፍላቂት ገረገራ ገንዘብ ጽ/ቤት/ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ግዥ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ስራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 16ኛው ቀን 3፡00 ድረስ በሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በአንዱ ሎት ውስጥ የተዘረዘሩትን የእቃ አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይችልም፡፡
- እንደ በጀት አቅም 20 በመቶ የመቀነስና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በእያንዳንዱ ምድብ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት መስፈርቱን ከጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ነው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም በ16ኛው ቀን 3፡00 ተዘግቶ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ስዓት ተዘግቶ በዚሁ ስዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 በሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ለፍ/ገ/ከአስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት በማስያዝ ውሉን መፈጸም ይኖርበታል፡፡ በተባለው ቀን ውሉን የማይፈጽም ከሆነ ያስያዘው የውል ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ውል ከፈጸመ በኋላ የአሸነፋቸውን እቃዎች በፍላቂት ገረገራ ከ/አስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት ድረስ አጓጉዞ ያቀርባል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033 211 05 28 እና በ033 211 00 89 በመደወል መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡
የፍላቂት ገረገራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

