የመሬት ሊዝ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
38

በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት በ2018 የበጀት አመት የ2ኛ ሩብ አመት 1ኛ ዙር የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት የመኖሪያና የሆቴል አገልግሎት የሚውሉ የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለአሸናፊዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለመጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ግለሰብ ከህዳር 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ ለመኖሪያ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/፣ ለሆቴል ብር 400 /አራት መቶ ብር/ የማይመለስ በመክፈል እና የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) 35 በመቶ በማስያዝ በከተማ አስተዳደሩ ቅጥር ግቢ ቢሮ ቁጥር 76 ድረስ በመምጣት ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

  1. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከህዳር 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 19/2018 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
  2. ጨረታው የሚዘጋው ህዳር 19/2018 ዓ.ም ከቀኑ በ11፡00 ይሆናል፡፡
  3. ቦታውን መጎብኘት ለምትፈልጉ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሀ-ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው ህዳር 22/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡00 በከተማ አስተዳደሩ ቅጥር ግቢ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
  5. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 058 775 17 75 በመደወል ወይም ቢሮ ቁጥር 76 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የፍኖተ ሰላም ከተማ አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here