ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
48

በሰሜን ጎጃም ዞን የሰሜን አቸፈር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በመደበኛ በጀት ለሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኑክስ፣ ሎት 3 ጽዳት እቃዎች እና ሎት 4 ጀነሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የአገልግሎት ግዥውን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለሎት 1 ብር 15,000 ፤ ለሎት 2 ብር 20,000 እና ለሎት 3 ብር 4000 ለሎት 4 ብር 7,000 ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ከሰሜን አቸፈር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ዋና ገ/ያዥ ላይ በመክፈልና የከፈሉበትን ማስረጃ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋራ በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ተሽጦ በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች ኦርጅናል እና ኮፒ የመጫረቻ ሰነዶችን ከጨረታ ማስከበሪያ ጋር በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን በሰሜን አቸፈር ወረዳ ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. አሸናፊው ተጫራች የሚመረጠው ባቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ስለሆነ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የሚገኙትን የሁሉንም ዋጋ መሙላት ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ሙሉ በሙሉ ከጨረታው ውጭ ይደረጋል እንዲሁም የሚሞላውን ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ እና የሞላውን ዋጋ ቫትን ጨምሮ ወይም ከቫት ውጭ መሆኑን መግለጽ ይኖርበታል፤ ካልተፃፈ ግን የተሞላው ዋጋ ቫትን እንደሚጨምር ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በየሎቱ በመክፈል ከሰ/አቸ/ወ/ግ/ን/አስ/ቡድን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  11. መ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ ከ20 በመቶ ቀንሶም ይሁን ጨምሮ መግዛት ይችላል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ተጫራቾች ዋጋ በሚያስቀምጡበት ጊዜ የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ ሁሉን የጨረታ ሰነዶች ፖስታው ላይ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የሚሞሉት ዋጋ ሥርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ መሆን የለበትም ሆኖም ግን ሥርዝ ድልዝ ካለው ፊት ለፊት ፓራፍ ወይም መፈረም ይኖርባቿል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ተጫራቾች ሙሉ በሙሉ ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ፡፡
  14. ተጫራቾች በጨረታዉ ተወዳድረዉ አሸናፊ ከሆኑ እቃዎችን የሚያቀርቡበት ቦታ ሰሜን አቸፈር ወረዳ ሊበን ከተማ ሲሆን የጭነት እና የጫኝ አዉራጅ ሙሉ ወጭ የሚሸፍኑ ይሆናል፡፡
  15. ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዩች በግዥ አፈጻጸም መመሪያው መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
  16. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 05 በአካል በመገኘት በስልክ ቁጥር 058 890 93 75 ደዉለዉ ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡

የሰሜን አቸፈር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here