ግልጽ የጨረታ  ማስታወቂያ

0
28

በደቡብ ወሎ ዞን በተንታ ወረዳ የአጅባር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 በጀት አመት የሚያስፈለጉትን የደንብ ልብስ ፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ኤሌክትሪክ ሲቲ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆንም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ለመሆኑ ማረጋገጫ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት  ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምሰክር  ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘዉ ማቅረብ  አለባቸዉ፡፡
  4. የሚገዙትን እቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል  ከአጅባር ክኒክ ኮሌጅ  ግዥ//ንብ/አስ/ቡድን  ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ  በባንክ  በተረጋገጠ  የክፍያ  ትዕዛዝ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ  ማስያዝ  አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ  ከሆነ  በመ/ቤቱ ህጋዊ  ደረሰኝ  ገቢ ተደርጎ  ካርኒው ከሰነዱ ጋር አብሮ  ከሳጥኑ  ውስጥ መግባት አለበት፡፡ ደረቅ ቼክ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  7. አሽናፊው የሚለየው በጥቅል (በሎት) ዋጋ በመሆኑ ተጫራቾች ሁሉንም ዝርዝር ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡
  8. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት  ቀን በኋላ የውል ማስከበሪያ  ካሸነፈበት  ከጠቅላላ ዋጋ  25 በመቶ  በጥሬ ገንዘብ  ወይም በባንክ  በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  9. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በአጅባር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዉስጥ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን  ጀምሮ በ16 ተኛዉ  ቀን ከጠዋቱ 330 ታሽጎ  400 በይፋ ይከፈታል፡፡ የሥራ  ቀን  ካልሆነ  በሚቀጥለው ቀን  በተመሳሳይ   ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች  ሃሳቡን  በጥንቃቄ  በታሸገ  ፖስታ  አጅባር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግዥ//ንብ/አስ/ቡድን  ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 330 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ 
  11. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን እቃ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ድረስ በራሱ ወጭ ማቅረብ አለበት፡፡ በተጨማሪም የሚቀርቡ እቃዎች በባለሙያ እየተረጋገጠ  የምንረከብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  12. የሚገዙት እቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ እንድሁም የሚጠየቁትን  ናሙና  ማቅረብ  ይጠበቅባቸዋል፡፡
  13. በጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ  በሌለበት  ሁኔታ መሞላት አለበት፡፡ ሆኖም ሥርዝ ድልዝ  ካለው ስለመስተካከሉ ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
  14. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ  ካገኘ ጨረታውን  በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ  በህግ የተጠበቀ ነው
  15. /ቤቱ በጨረታው  በቀረቡ  እቃዎች  መጠን  20 በመቶ  የመጨመርና  የመቀነስ መብት አለው፡፡
  16. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ግዥ ክፍል ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 441 04 70 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  17. በዚህ ጨረታ ያልተገለፁ ጉዳዮች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ 

አጅባር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here