በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮሃንስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 ስቴሽነሪ፣ ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 4 ፈርኒቸር፣ ሎት 5 የመኪና ጎማ እንዲሁም ሎት 6 የመኪና ዘይትና ቅባት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋያ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅርብ የሚችሉ፡፡
- የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግሰጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዝርዝር መገለጫው የቀረቡትን እቃዎች ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው፡፡
- የዚህ ጨረታ ሰነድ ህዳር 01/ 2018 ዓ/ም አስከ ህዳር 15/2018 ዓ/ም ድረስ ዘውትር በሥራ ሰዓት ከጠዋት 1:30 እስከ 6፡30 እና ከሰዓት ከ9፡00 አስከ 12፡00 ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በመተማ ዮሃንስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ/ትብ/ጽ/ቤት ቢሮ 02 የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ መዉሰድ ይችላሉ፡፡
- የአንድ ሰነድ መግዣ ዋጋ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ መሆኑን እንገፃለን፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በመ/ዮ/ገ/ኮ/ትብ/ጽ/ቤት በግ/ፋ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 02 ህዳር 16/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡30 የታሽገዉ ፖስታ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀን ተጫራቾች ባይገኙም የማይስተጓጎል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታዉ ሂደት በሚተላለፉ ዉሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ውል የሚወስደው በመ/ዮ/ከ/አስ/አቃቢ ህግ ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
- ማንኛውም አሽናፊ ድርጅት አሽናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ የሚፈለጉትን ዕቃዎች የትራንስፖርት ማጓጓዣና እንዲሁም ሌሎች ዉጭዎች በራሳቸው የሚሸፈን ሆኖ እቃው (ስፔስፊኬሽን) ችግር ቢኖርበት በራሳቸው ትራንስፖርት የሚመለስ ይሆናል፡፡ ውል ከተያዘ በኃላ የሚፈለጉትን ዕቃዎች በሚፈለገው ጊዜ ባያቀርብ ያስያዙትን የውል ማስከበሪያ ውርስ ሆኖ በህግ የሚጠየቁ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተጠቀሰውን ዕቃ 20 በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብት አለው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 555 55 05 /09 18 73 77 76 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የመተማ ዮሃንስ ከተማ አስተዳር ገንዘብ ጽ/ቤት

