በደበብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የሊቦ ከምከም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሊቦ ከምከም ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3 የመኪና ጎማ እና ሎት 4 የጽዳት እቃዎች ከተጫራቾች መካከል በማወዳደር በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፈቃዱን ያደሱ፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር እያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሊቦ ከም/ወ/ገ/ኢ/ል ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) 1.5 በመቶ የጠቅላላውን ድምር ዋጋ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ከሆነ የገቢ ደረሰኝ መቁረጥ እና ከሰነዱ ጋር ኮፒ መያያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት እስከ 11፡30 ይቆያል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሊቦ ከምከም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብ/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁ 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን የጨረታ ማስከበሪያውን ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር ፖስታ ውስጥ በማድረግ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከተዘጋጀው ሳጥን እስከ 15 ኛው ቀን ድረስ እስከ 11፡30 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚያው ቀን 11:30 ላይ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት ባይገኝ የጨረታውን መክፈት የማያስተጓጉለው ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለተላለፉ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
- አሽናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ አለበት፡
- መ/ቤቱ ከሚገዛው እቃ ግዥ ላይ 20 በመቶ ከፍና ዝቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው አካል የሚለየው በጥቅል ነው፡፡
- አሸናፊው አካል ያሸነፈውን እቃ ሊቦ ከምከም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማድረስ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጨረታ በእያንዳንዱ ሎት በቀረበው ሳምፕል መሰርት መሙላት አለባቸው፡፡
- ጨረታውን ሥርዝ ድልዝ ሳይኖረው እና እንዲነበብ ተድረጎ መሙላት አለበት፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ሁሉም ሎቶች በተጠየቁት ጥራት (ስፔስፊኪሽን) መሰረት በባለሙያ ተፈተሾ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 444 01 95 /931 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሊቦ ከምከም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

