በአፈ/ከሳሽ የኋላ ጋሼ እና በአፈ/ተከሳሽ አቶ አያና ምህረት መካከል ባለዉ የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ 01 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ አሳየ መብራት፣ በሰሜን መህቶት አበራ እንዲሁም በደቡብ ቄስ ብርሃን ምህረት የሚያዋስነው በአፈ/ተከሳሽ በወ/ሮ ሲሳይ አያና ደስታ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መኖሪያ ቤት የሆነው በመነሻ ዋጋ ብር 2,350,000 /ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ ይሸፃል፡፡ በመሆኑም የጨረታ ማስታወቂያ ከህዳር 01/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 30/2018 ዓ.ም ድረስ በጋዜጣ ወጥቶ ቀይቶ መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ¼ ኛው ብር በባንክ ሲፒኦ አስይዞ የመቅርብ ግዴታ ያለበት መሆኑን አውቆ ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5:00 ድረስ ቀርቦ መጫረት የሚችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍ/ቤት

