ለሻሁራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ማለትም ሎት 1 የደንብ ልብስ፣ ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 3 አላቂ የጽዳት አቃዎች እና ሎት 4 የኤሌትሮኒክስ እቃዎች በገልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በዘርፍ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና (ቲን) ያላቸው፡፡
- የገዥ መጠኑ ከመቶ ሽህ ብር በላይ ከሆነ የተጫማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር በወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ የሰነድ መግዣ ዋጋ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒውን በሁለት በታሸገ ኢንቨሎፕ ፖስታ በጥንቃቄ ተሞልቶ በሻሁራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከህዳር 01/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 15/2018 ዓ.ም ለ15 ቀን ተከታታይ በጋዜጣ ወጥቶ ቀይቶ በህዳር 15/2018 ዓ.ም በ11፡00 ጨረታ ሳጥኑ ይታሸገና በህዳር 16/2018 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት በሻሁራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል 3፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ዕቃውን በራሱ ትራንስፖርት ማምጣትና በጥራት ኮሚቴ አስገምገሞ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- አሸናፊ የሚለየው በድምር ነው፡፡
የሻሁራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

