ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
47

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የተስፋየ ጌታቸው መታሰቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለ2018 ዓ.ም በግቢው ውስጥ የጥገና ሥራዎችን (የበር መግቢያ፣ ኮርኒስ ስራ፣ የመኪና ፓርኪንግ፣ ከኮሊደር ቢሮና በር ማውጣት፣ የደረቅ ቆሻሻ ማቃጠያ ጉድጓድ፣ እና የወላጆች አልጋ ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈለጋል፡፡ ማንኛውንም የጥገና ማቴሪያል አቅርቦት እና የጉልበት ሥራ በተቋራጩ የሚሸፈን ይሆናል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት የሚፈለግባቸው መስፈርቶች፡-

  1. ህጋዊ /ወቅታዊ/ የታደሰ የዘርፍ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውንና ሌሎች መረጃዎችን በፖስታ በማሸግ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለስራዉ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡20 ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ሙሉ አድራሻቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ እና ካሸነፈ በኋላ 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ ማቅረብ የሚችል፡፡
  8. ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የተ/ጌ/መ/የመ/ደ/ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 30 ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ከፍሎ ከዋና ገንዘብ ያዥ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  9. የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኃላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  10. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም በመንግስት የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፍ የሚደርጉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  11. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. አሸናፊውን በመወዳደሪያ ሰነዱ ላይ ባስቀመጠው ስልክ እና በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለፅ ይሆናል፡፡
  13. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ተነባቢ እና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን አለበት፡፡
  14. አርቲሜቲክ ቸክ ሲሰራ ከማህንዲስ ግምቱ ከተቀመጠው ዋጋ 25 በመቶ ዝቅ ብሎ የሞላ ተጫራች የውል ማስከበራያ 25 በመቶ ያስይዛል፤ የቅድሚያ ክፍያ አይፈቀድለትም፡፡
  15. በጠቅላላ የህንፃ ስራ ተቋርጭ የዘርፉ ፈቃድ ያላቸው ደረጃ 6 እና በላይ መወዳደር ይችላሉ፡፡
  16. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፍታል፡፡
  17. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  18. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 667 06 35 ደውለው ወይም ቢሮ ቁጥር 04 በአካል መጥቶ መጠየቅ ይችላል፡፡

የተስፋየ ጌታቸው መታሰቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here