በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሎት ı የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃ እና ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና በተናጠል የኮንስትራክሽን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራቾች እቃዎችን ወይም አገልግሎቾችን ለማቅረብ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያወጡ የተሰጣቸው ፈቃድ አንድ አመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት ሙቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ከገንዘብ ያዥ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማርኛ መሆን ይኖርበታል፡፡
- በዚህ ጨረታ መጫረት የምትፈልጉ በማያሻማ ሁኔታ በመሙላት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- አንድ ተጫራች በወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ቢያስፈልገው ጨረታውን ላወጣው መስሪያ ቤት በፅሁፍ ወይም በፋክስ ቁጥር 058 661 02 64 ወይም በስልክ ቁጥር 058 661 03 30 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤትም የተጠየቀውን ጥያቄ ማብራሪያ የሚያሰጥ ሆኖ ሲገኝ ለሁሉም ተጫራቾች በጽሁፍ ወይም በፋክስ ጨረታው ከመከፈቱ ከ5 ቀናት በፊት መልስ ይሰጣል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን እሁድ ቅዳሜና በዝግ ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተጠየቀው ስዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አሸናፊ ከተለየ በኋላ የሚመለስ ለእያንዳንዱ ሎት እና ለተናጠሉ ጨረታ ብር 4,000 /አራት ሽህ ብር/ ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
የሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል

