የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል በሥሩ ለሚገኙ የሥራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1.የጽ/መሳሪያ፣ሎት 2.የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፣ ሎት 3 የጽዳት እቃዎችን፣ ሎት 4 የፈርኒቸር እቃዎችን፣ ሎት 5 የሰራተኛ ድንብ ልብስ፣ ሎት 6 የኤሌክትሪክና የግንባታ እቃዎችን፣ ሎት 7 የመኪና ጎማ እና ሎት 8 የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ውል ይዞ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመምጣት ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 በመቁረጥ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በ 2 ፖስታ በማሸግ ዋናና ቅጅ በማለትና በማሸግ ሙሉ ስም ፣የድርጅቱ ማህተም፣ አድራሻውን ከፖስታው ላይ በመፃፍ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመ/ቤታችን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባችዋል ፤ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ህዳር 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ጨረታው በ16ኛው ማለትም ህዳር 16/2018 ዓ.ም ጠዋት 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ሥርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የተስተካከለ ከሆነ ሰነዱ ተቀባይነት የለውም ወይም መፈረም አለበት፡፡
- አሸናፊው በውሉ መሰረትና በወጣው ስፔሲፊኬሽን በባለሙያ ተረጋግጦ የሚያስረክብ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾቹ ከዚህ በፊት በአገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታ ያልቀረበበት መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል፤ ጨረታው ሲከፈት ያልተገኙ ተጫራቾች በዕለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- ጨረታ የሚከፈትበት ቀን ብሄራዊ በዓል ከሆነ ለሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ አሸናፊው ድርጅት ላይ ከተጠቀሱት ዕቃዎች ብዛት ላይ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የማሰራት መብቱ እንደተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ አሽናፊውን የሚለየው በጥቅል ድምር /በሎት/ ዋጋ ይሆናል፤ በመሆኑም ተጫራቾች ሁሉም በጨረታው የተቀመጡትን ዝርዝር ዋጋ ሙሉ ለሙሉ በጥንቃቄ መሙላት ይጠበቅባችዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 22 05 04 /09 18 21 06 28 /09 23 22 10 87 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል

