የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
85

በአብክመ ጤና ቢሮ የባሕር ዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አገልግሎት የሚውሉ በ2018 በጀት አመት የሚፈጸሙ የግዥ አይነቶች፡- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 ህትመት፣ ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ፣ ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 6 ፊርኒቸር ፣ ሎት 7 የተሸከርካሪ ማስዋቢያዎች ፣ሎት 8 የጥገና እቃዎች ፣ ሎት 9 Chemicals/Reagents፣ ሎት 10 Medications and Supplies፣ ሎት 11 Equipment እና ሎት 12 የስፖርት መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች (ድርጅቶች) መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በየሎቱ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግዥ ንብ /አስ/ደ/የስራ ሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 05 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚወዳዳሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ባሕር ዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 16ተኛዉ ቀን 2፡15 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዚሁ እለት 2፡30 ታሽጎ በድጋሚ በዚሁ እለት 3፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ከመከፈት አያስተጓጉለውም ፡፡ የመክፈቻው ቀን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  10. ጨረታው በሎት ስለሚታይ ተጫራቾች ሁሉንም በሎቱ የተገለፁትን ዝርዝር መሙላት አለባቸው፡፡

ከሎቱ ውስጥ አንዱን ያልሞላ አጠቃላይ ከጨረታ ውድቅ ይሆናል፡፡

  1. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  2. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 058 220 07 71 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. ኮሌጁ ከፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል 100 ሜትር ገባ ብሎ ከኦክስጅን ማቀነባበሪያ ጎን ይገኛል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ዉድድሩ የሚካሄደዉ ጠቅላላ የሎቱ ድምር ስለሆነ ተወዳዳሪ ድርጅቶች በሰነዱ ላይ ያሉትን የእቃ ዝርዝሮች በሙሉ መሙላት ይጠበቅባችኋል፡፡

የባሕር ዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here