ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
55

በሰሜን ጎንደር ዞን የደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል በመደበኛ በውስጥ ገቢ እና Susan Thompson Buffet Fundation የበጀት ምንጭ ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን እና ግንባታ ጥገና በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1  የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ብትን የደንብ ልብስ፣ ሎት 4 የተዘጋጁ የደንብ ልብሶች፣ ሎት 5 የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ሎት 6 ኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች እንዲሁም ሎት 7 ግንባታ ጥጋና የማዋለጃ ክፍል አልሙኒያም ፓርቲሽን የውሰጥና የውጭ የቀለም እድሳት፣ የመፀዳጃ ቤት፣ ሻወር፣ የእጅ መታጠቢያ እና መፋሰሻ ቦዮች ጥገና /Facility WASH/ የተሰባበሩ በር መስኮት ኮረኒስ፣ የኤሌክትሪክ መብራቶች፣ ሶኬቶች፣ ማብሪያ ማጥፊያዎች እድሳት እና ጥገና ተጫራቾች ማሟላት የሚችሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
  4. ከላይ ከተራ ቁጥር 1-7 የተዘረዘሩትን እያንዳንዱን መግዛት የሚፈልጉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት የሚነበብ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  5. የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው ጨረታው ከወጣበት ከህዳር 1/2018 ዓ/ም እስከ ህዳር 15/2018 ዓ/ም ድረስ ለ15 ተከታታይ ቀን በጋዜጣ ወጥቶ ይቆያል፡፡
  6. ጨረታው በቀን ህዳር 16/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 በደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 62 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱ ለሚወዳደሩበት የእቃ አይነት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 62 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ የሌለበት እና በሰነዱ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን የድርጅቱ ማህተም መቀመጥ አለበት፡፡
  9. ጨረታው የሚታየው በሎት ስለሆነ ከጨረታ ሰነዱ ያሉ ሁሉንም እቃዎች መሞላት ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የሚሞሉት የጨረታ ሰነዶች በኦርጅናል እና በኮፒ ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብረዉ መግባት ይኖርበታል፡፡
  10. የጨረታ ማስከበሪያ (በሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ጥቅል ዋጋ ብር 3000 /ሶስት ሽህ ብር/ በየሎቱ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ጥሬ ገንዘብ ሆነ ቼክ አያይዞ ከጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ከዉድድር ዉጭ ያደርጋል፡፡
  11. በሎት 7 የቀረበው የግንባታ ጥገና ተሳታፊዎች ደረጃ BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆነ እንዲሁም የግንባታ ጥገና ዋጋ ለጥገና የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን እና የእጅ ዋጋውን ያጠቃልላል፡፡
  12. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ /ጥገና ውል እንዲወስድ በተጠየቀ ጊዜ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በፍትህ ፊት ቀርቦ ውል መውሰድ ይኖርበታል፡፡
  13. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈዉን እቃ ጥገና ደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል በማምጣት የሚያስረክብ መሆን አለበት፡፡
  14. የጨረታ መዝጊያ ጊዜው ከተጠናቀቀ በኋላ የሚመጣ ፖስታ ዋጋ አይኖረውም፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 117 05 12 ወይም 058 117 00 39 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here