በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን በሊቦ ከምከም ወረዳ የአዲስ ዘመን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሎት 1 የጽ/መሳሪያ ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3 ሌሎች አላቂ ዕቃዎች (የመብራት አምፖሎች የውሃ ዕቃዎች)፣ ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ኮፒዩተሮች)፣ ሎት 5 ሌሎች ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች (ሸልፎች ጠረጴዛዎች ካዝናዎች ወ.ዘ.ተ)፣ ሎት 6 የግንባታ እቃዎች፣ሎት7 የደንብ ልብስ ግዥ፤ ሎት 8 የህትመት አገልግሎት ግዥ አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ ከአቅራቢዎች መካከል አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የገዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ለሆነ ግዥዎች የተጨማሪ አሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተዘረዘሩትንና የሚመለታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ኦርጅናል ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ለእያንዳንዱን ሎቶች ብር 40 /አርባ ብር/ በአንድ ሰነድ ውስጥ አንድ ሰነድ ብቻ ለሚገዛ ብር 20 /ሃያ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 9 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የዕቃውን (አገልግሎት) ግዥ የተጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ኮፒውን ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአዲስ ዘመን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በግ/ፋ/ን/ቡ መሪ ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ16 ተኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3:00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት (በሌሉበት) በሆስፒታሉ የመስብሰቢያ አዳራሽ ቁጥር 01 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 03፡15 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ በህግ የተከለከለ ነው፡፡
- መ/ቤቱ በጨረታ ዋጋ መጠን ላይ እስከ 20 በመቶ የመቀነስና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ቢሮ ድረስ በአካል በገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 141 03 71 /09 18 64 54 02 /09 18 61 70 63 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአዲስ ዘመን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

