በደብረ ጽባሕ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰበካ ጉባዔ ሥር በሚተዳደረው በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን በጭቃ የተሰሩ ቤቶችንና ቀደም ሲል በነበረው የመሬት መቃብር ዳር ዳር ያሉ ሐውልቶች ተነስተው ቦታ ቆጣቢ እና ብዙ ሕዝብ በሚስተናገድበት አግባብ ማሕበረሰቡን ለማስተናገድ ሰበካ ጉባኤው ጥቅምት 18/2018 ዓ/ም ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በመሆኑም በተፈለገው ቦታ ላይ ያሉ የጭቃ ቤቶችና ሐውልቶች እንዲፈርሱና በሚሰጣቸው ተለዋጭ ቦታ አጽሙን እንዲያነሱ ማለትም በቤተክርስቲያን በአውደ ምህረት በተከታታይ ማስታወቂያ ስናስነግር ቆይተናል፡፡ ስለሆነም የቤተሰቦቻቸውን አጽም እስከ ሕዳር 20/2018 ዓ/ም መጥተው እንዲያነሱልን እየገለፅን እስከተጠቀሰው ቀን ድረስ የማያነሱልን ከሆነ የደብሩ ሰበካ ጉባዔ ከዚህ ጋዜጣ እወጃ በኋላ ቤቶቹንና ሐውልቶቹን በማፍረስ አጽሙን በአግባቡ አመቺ ቦታ ላይ እንዲቀመጥ ለማድረግ የሚገደድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 681 20 36 ደውለው መረጃ ማግኙት ይችላሉ፡፡
በደብረ ጽባሕ ቅ/ጊዮርጊስ መካነ ሰማዕት ቅ/ቂርቆስ ቤተክርስቲያን አንድነት ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት

