ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
84

አማራ ልማት ማሕበር (አልማ) በአጋርነት አብረው ለሚሠሩ ወጣት- መር እና ማህበረሰብን መሠረት ያደረጉ ድርጅቶች (Youth-Led and Grassroots Organizations) የፍላጎት ማሳወቂያ ማስታወቂያ /Call for Expression of Interest አማራ ልማት ማህበር /አልማ/ ሀገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ የህዝብ ልማት ማህበር ነዉ፡፡ አልማ በአማራ ክልል በራስ መተማመን መርህ በህዝብ ተሳትፎ የሚተገበር ልማት እንዲኖር ይጥራል፡፡ ለዚህ ዓላማዉ ማስፈፀሚያ ከህዝብና ከበጎ አድራጊ ግለሰቦች እንዲሁም ከለጋሽ ድርጅቶች ሀብት በማሰባሰብ ለልማት ሥራ ያዉላል፡፡ በልማቱም የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በዚህም መሠረት ማህበራችን በደቡብ ጎንደር ዞን ውስጥ በሚገኙ አራት ወረዳዎች (አዲስ ዘመን እና ወረታ ከተሞች እንዲሁም በሊቦ ከምከም እና ፎገራ ወረዳዎች) ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ የሙከራ ፕሮጀክት ለመፈፀም ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ የፕሮጀክት ተግባራት በሙሉ የሚፈፀሙት በየአካባቢዎች በሚገኙ በወጣቶች በሚመሩ ወይም ማህበረሰብን መሠረት ያደረጉ ድርጅቶች ማለትም ማህበር፣ ኢንተርፕራይዝ፣ መያድ፣ ብድርና ቁጠባ ህብረት ሥራ ማህበር ወዘተ ሲሆን፤ አልማ በአጋርነት አብረው ለመሥራት ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶችን አወዳድሮ በአጋርነት በትብብር ለመሥራት ይፈልጋል፡፡

ዓላማ፡- ይህ የፍላጎት ማሳወቂያ ማመልከቻው ዋናው ዓላማ የወጣቶች የሥራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክትን ለመተግበር የሚችሉ በወጣቶች የሚመሩ ማህበራትን ወይም መያድን ወይም ኢንተርፕራይዞችን ወዘተ ለመምረጥ ነው፡፡ እነዚህ የሚመረጡ ድርጅቶች ከማህበረሰብ ወኪሎች ጋር በመተባበር ግልጽ የሆነ የመመልመያ መስፈርት አዘጋጅቶ በአካባቢው የሚገኙ እና በኢኮኖሚ የተጎዱ ወጣቶችን በመመልመል ወደ ሥራ እንዲገቡ ማገዝ ሲሆን፤ ለዚህ የሥራ ማስፈፀሚያ ደግሞ በክልል እና በየወረዳው በሚቋቋሙ የቴክኒክ ኮሚቴዎች ጋር በመተባበር የሚተገበር ይሆናል፡፡ ከፕሮጀክቱ የሚጠቀሙ ወጣቶች  80 በመቶ ሴቶች፣ 5 በመቶ የአካል ጉዳተኞች፣ 5 በመቶ የተለየ ችግር የገጠማቸው ለምሳሌ ከሌላ አካባቢ ተሰደው የመጡ እና 10 በመቶ ደግሞ ወንድ ወጣቶች መሆን እንዳለባቸው ይጠበቃል፡፡ ፕሮጀክቱ የሚያተኩረባቸው የሥራ ዘርፎች፡-

  1. አቀባዊ የአትክልት ልማት እና የከተማ ግብርና /Vertical Gardening
  2. አረንጓዴ ልማት /የፀሐይ ኃይል ልማት /Innovative Green Solutions/ Solar Energy
  3. እንስሳት እርባታ እና ማድለብ /Livestock Rearing and Fattening/
  4. የዶሮ እርባታ /Poultry Farming/ በዚህም መሠረት መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካች ድርጅቶች የፍላጎት ማሳወቂያ ማመልከቻ ቅጹን ከታች በተዘረዘሩት የአልማ ጽ/ቤቶች በመውሰድ በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ መልስ በመስጠት ከሸኝ ደብዳቤ ጋር በማዘጋጀት ከዚህ በታች በተገለፀው አደራሻ እና ቀን የአጋርነት ፍላጎታቸውን መስጠት ይችላሉ፡፡

አመልካች ድርጅቱ ሊያሟላ የሚገባቸው መስፈርቶች

  1. ከተቋቋመ አንድ ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነና ህጋዊ ምዝገባ እና ፈቃድ ያለው፡፡
  2. በወጣቶች የተመሰረተ እና በወጣቶች የሚመራ ወይም ማህበረሰብን መሠረት ያደረገ አገር በቀል ድርጅት የሆነ፡፡
  3. የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ የሙከራ ፕሮጀክት ተግባራትን ለመፈፀም ፍላጎቱ እና ተነሳሽነት ያለው፡፡
  4. የሚወዳደርበትን ወረዳ (ዎች) ጠንቅቆ የሚያውቅ፡፡
  5. ፕሮጀክቱ የሚያተኩረባቸው የሥራ ዘርፎች ላይ ከዚህ በፊት ልምድ ያለው ቢሆን ይመረጣል፡፡

የፍላጎት ማሳወቂያ ማመልከቻ ማቅረቢያ ቦታ እና ቀን ማመልከቻ ማቅረቢያ ቦታ

  1. አልማ ዋናው መ/ቤት ባሕር ዳር ከተማ አንደኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 100 ወይም ደቡብ ጎንደር አልማ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ ደብረ ታቦር ከተማ ፒተር ህንፃ ሁለተኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 01፣ አዲስ ዘመን ከተማ አልማ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ወይም ወረታ ከተማ አልማ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት

የፍላጎት ማሳወቂያ ማመልከቻ ማቅረቢያ ቀን ከጥቅምት 27/2018 እስከ ሕዳር 11/2018 ዓ.ም ከሰኞ እስከ ዓርብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  1. የወጣቶች የእድሜ ክልል ከ18-35 ነው፡፡
  2. ፕሮገራሙ ሰባት ድርጅቶችን መልምሎ በአጋርነት መሥራት ይፈልጋል፡፡
  3. ፕሮግራሙ ለሚመረጡት ፈፃሚ ድርጅቶች ለወጣቶች የሥራ እድል መፍጠሪያ የሚውል የገንዘብ ድጋ የሚያደርግ ሲሆን፤ በሁለት ዓመት የፕሮግራሙ ጊዜ ውስጥ እንደየአፈጻጸሙ እየታየ የተለያዩ የአቅም ግንባታ እና የክትትል ድጋፎችን ያደርጋል፡፡
  4. አመልካቾች የታደሰ የምዝገባ ፈቃድ፣ የመጨረሻ የኦዲት ሪፖርት እና የመተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎች ካሉ ከማመልከቻ ቅጽ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 18 76 64 38 ወይም 09 18 78 35 93 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡

አማራ ልማት ማህበር (አልማ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here