በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውኃናኢነርጅ ቢሮ በዩኒሴፍ የበጀት ምንጭ የአንዳሳ መጠጥ ውሃ ማስፋፊያ አገልግሎት የሚውል የHDPE ቧንቧ አቅርቦት ግዥ የጨረታ ሰነድ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየጋበዝን፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች ዕቃውን (አገልግሎቶችን) ለማቅረብ በዘርፉ (የኤሌክትሮ_መካኒካልና የቧንቧ ዕቃዎች አቅራቢነት) ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በውሀና ኢነርጅ በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺብር ብቻ/ በመክፈል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሃና ኢነርጅ ቢሮ ቁጥር 23 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ 100,000 ብር /አንድ መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ /ሲፒኦ /ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከህዳር 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን የጨረታው መዝጊያ ቀን ደግሞ ህዳር 15/2018 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን በዚሁ ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብአት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያ ቀን በዓል ከሆነ በተመሳሳይ ሰዓት በቀጣዩ የስራ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን የሚያቀርቡት በተሸጠላቸው የጨረታ ሰነድ (ቅጽ) ብቻ መሙላት ይኖርበታል፡፡
- ሌሎች ተጫራቶች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ቢሮው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251582-26-24-60/+251 582-20-10-87/+251 582-20-08-55 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአብክመ የውኃናኢነርጅ ቢሮ

