ዴይ ፎረስት ብሔራዊ ፓርክ

0
268

ዴይፎረስት ብሔራዊ ፓርክ በጅቡቲ ሰሜናዊ ቀጣና በጐዳ ተራሮች እና ታጁራ ክልል ነው የሚገኘው:: አገሪቱ ካሏት ሁለት ፓርኮች በስፋቱ ቀዳሚ ነው:: አጠቃላይ ስፋቱም 15 ኪሎ ሜትር ስኩዌር ተለክቷል:: የምስረታ ጊዜውም በ1939 እ.አ.አ ነው::

ከጅቡቲ ከተማ ወደ ብሔራዊ ፓርኩ ለመድረስ በተሽከርካሪ 60 ኪሎ ሜትር፤ ለሁለት ሰዓት መጓዝን ግድ ይላል::

በፓርኩ ቀጣና የሚገኘው ደን አገሪቱ ካላት የደንሽፋን አብዛኛውን በመያዙ ተጠቃሽ ቢሆንም በዓለማችን በደን ሽፋን አነስተኛ መጠን ካላቸው አገራት መካከል ነው የምትመደበው- ጅቡቲ::

ፓርኩ በሰሜናዊ አፍሪካ ወይም ከሳሀራ በላይ ቀደም ባሉት ክፍለ ዘመናት ከነበረው እና ከውድመት የተረፈ የጥድ፣ የዱር ወይራ፣ እና የቁጥቋጦዎች መገኛ ነው:: በፓርኩ ከዱር እንስሳት ዝንጀሮ እና የሜዳ ፍየል፣ ከተሳቢ እንስሳት  እባብ እና የተለያዩ የሞቃት ቀጣና የእንሽላሊት ዝርያዎች ይገኙበታል::

ከዓዕዋፍ በአገሪቱ የሚታወቁት “ፍራንኮሊን” የተሰኙ ዝርያዎች በብዛት ይገኛሉ:: በተጨማሪም  ባለ አረንጓዴ ክንፍ ፒቲሊያ እና ፍላይካቸርንም አቅፏል::

ፓርኩን ለመጐብኘት ሙቀቱ በማያይልበት መጠነኛ ዝናብ በሚጥልበት ከጥቅምት እስከ ሚያዚያ ያሉት ወራት ተመራጭ መሆናቸውን ድረ ገፆች አስነብበዋል::

ከየትኛውም ቦታ  ወደ ፓርኩ ለሚያቀኑ ጐብኚዎች በዋና ከተማዋ ጅቡቲ ወይም ቡታጁራ ከተማ ባናዲር ሆቴል እና የጅቡቲ ቤተመንግሥት “ኬምፒንስኪ” የተሰኙ ለማረፊያነት ዝግጁ ሆነው እንደሚጠባበቁ ድረገፆች አስነብበዋል::

ለዘገባችን በመረጃ ምንጭነት ናሽናል ፓርክ አሶሴሽን፣ ዋይልደርነስ ኤክስፕሎር አፍሪካ፣ ዋይልደርንስ አፍሪካ እና ዋኪፒዲያ ድረ ገፆችን ተጠቅመናል::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here